ቤተ ክርስቲያን ይስጡ!!
ለቤተ ክርስቲያን የገንዘብ መስጠት፣ ስለት፣ መባ እና የአባልነት ክፍያ ለማድረግ የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ።
- በድረ ገጽ ለመስጠት Give የሚለውን ይጫኑ።
- በቼክ ለመላክ የቤተ ክርስቲያኑ አድራሻ 2601 Evarts St. NE Washington, DC 20018
- ስልክ በመደወል ለመክፈል (202) 269-0146
- በቀጥታ በቤተ ክርስቲያኑ የባንክ ለመላክ (For Direct Deposit) ዌልስ ፋርጎ ባንክ (Wells Fargo Bank) Account No. 1690560600 Routing No. 055003201
- በ Zelle ለመላክ የመደመር ምልክቷን በመክፈት Account No. 1690650600 First Name: Ethiopian Orthodox Tewahedo Ch Last Name: Debre Hail Kedus Gabriel Email: [email protected] ብለው በመሙላት መላክ ይችላሉ።
- በሐገራችን የሚደርሱ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለመርዳት እዚህ Donate ያድርጉ።
የእርዳታ ጥሪ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን እንርዳ!! በሐገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ሃብትና ንብረት አፍርተው ይኖሩ በነበሩ ወገኖቻችን ከነበሩበት ቀያቸው ማንነታቸውን መሠረት ያደረገ መፈናቀል፣ ሞትና ለረጅም ዘመናት ሰርተው ያፈሩትን ንብረታቸውን ለውድመት መዳረጉን በጀሮአችን ሰምተናል፤ በአይናችንም አይተናል። ጾታንና እድሜን ሳይለይ እጅግ ቀጥራቸው ብዙ በሆኑ ወገኖቻችን በተለይም አዲሱ የመንግስት የለውጥ አስተዳደር ከምጣ ጀምሮ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በዚህ በምንገኝበት ሃያ አንደኛ ክፍለ ዘመን በሰው ልጅ ያውም በራስ ወገን ይፈጸማል ተብሎ በማይታሰብ ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን ስናይ ይበልጥ የሚያሳዝንና ልብ የሚያደማ ሆኖ እናገኘዋለን። ይህ የወገኖቻችን የግፍ መከራና ስቃይ አሁንም ጭካኔና የአውሬነት ባህሪ በተላበሱ እኩያን አማካኝነት ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት በተለያዩ የሐገራችን ስፍራዎች በተለይም በመተከልና በኦሮሚያ ክልሎች ተባብሶ ቀጥሏል። በዚህም የተነሳ በእግዚአብሔር እርዳታና ጥበቃ ከአሰቃቂው ሞት የተረፉ ቁጥራቸው ከአንድ መቶ ሽህ በላይ የሚበልጡ ወገኖቻችን ተፈናቅለው በአገዋዊ ዞን አስተዳደር (ቻግኒ ከተማ አካባቢ) በተለያዩ ቦታዎች በጊዜያዊነት ተጠልለው ይገኛሉ። የተፈናቀሉ ዜጎቻችንን ለመርዳትና መልሶ ለማቋቋም መንግስትና በሀገር ቤት የሚገኘው ሕብረተሰባችን የሚያደርጉት ጥረት የሚያስመሰግን ቢሆንም ችግሩ በሁሉም የሐገሪቱ ቦታዎች በስፋት የተከሰተ በመሆኑ የእለት ጉርስ አጥተው የወገኖቻቸውን ድጋፍ የሚጠይቁ እጅግ ብዙ መሆናቸውን በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ተገልጿል። ምንም እንኳን በአለማችን የተከሰተው የኮቪድ ወረርሽኝ ያስከተለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር እጅግ ከፍተኛ ቢሆንም በሕይወት የተረፉትን ወገኖቻችን በዕርዳታ ማጣት ምክንያት በሞት እንዳናጣቸው ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ አቅማችሁ የሚፈቅደውንና የምትችሉትን ዕርዳታ እንድታደርጉ ቤተ ክርስቲያናችን ጥሪ ታቀርባለች።
ዕርዳታውን በሚከተሉት መንገዶች ይሰበሰባል።
- በቤተ ክርስቲያኑ ድህረ ገጽ Give የሚለውን በመምረጥ ቀጥለው ኢመርጀንሲ የሚለውን ይምረጡ።
- በቼክ ለመላክ Debre Hail Kedus Gabriel ብለው በመጻፍ በዚህ አድራሻ ይላኩሉን። 2601 Evarts St. NE Washington, DC 20018
- ዘወትር ከሰኞ እስከ እሁድ ከጧቱ 10 ሰዓት እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት በቤተ ክርስቲያኑ ስልክ ቁጥር (202) 269-0146 በመደወል ወይንም በአካል በመገኘት ዕርዳያ ማድረግ ይቻላል።
እግዚአብሔር አምላክ ለሐገራችን ሠላምና መረጋጋትን፤ ለሕዝባችን ደግሞ ፍቅርንና አንድነትን እንዲሰጥልን በያለንበት በጸሎት እንድንተጋ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ያሳስባል።
የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ
Our Belief
We believe in one God the Father almighty, maker of heaven, earth and all things visible and invisible. By Him all things were made, and Without Him was not anything in heaven or earth made.
Christening Service
Debre Hail Kedus Gabriel Ethiopian Orthodox Tewahedo Cathedral Christening Service starts Sundays exactly at 06:00 A.M. Please contact the clergy and the office administrator ahead of time. Please be there on time.
Wedding Service
Debre Hail Kedus Gabriel Ethiopian Orthodox Tewahedo Cathedral provides wedding services on Sundays from 10:00 A.M. to 12:00 P.M. The church will provide the religious service for the bride and groom. For further questions or explanation, please contact the church by phone, email or in person.
Memorial Service
Debre Hail Kedus Gabriel Ethiopian Orthodox Tewahedo Cathedral provides memorial service for orthodox believers who depart from this world. If you need further explanation or have questions regarding the service, please contact the church administrator.
Ask Your Queries
Call Us (202) 269 – 0146
Write Us [email protected]
Visit Us
2601 Evarts St. NE Washington, DC 20018
“በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፤ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፤ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።” ትንቢተ ሚልክያ 3:10
Give your vow, tithe, offering, donation, charity, emergency fund etc. here.
የአባልነት ቅጽ፣ የክርስትና ቅጽ እንዲሁም የስርዓተ ቅዳሴ መሳተፊያ ፎርሞችን እዚህ ያገኛሉ።